የወይዘሪት ብርቱካን ይቅርታና እስር አንድምታ

ሁለት ዓመታት ከተቃረበ እስር በኋላ በቅርቡ የተለቀቁት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀ መንበር ወ/ሪት ብርቱካን «ይቅርታ፥» ከእስር የተለቀቁበት ሁኔታና የእስር ቆይታ እያነጋገረ ነው።

ለመሆኑ የወ/ሪት ብርቱካን ከእስር መለቀቅ፥ አፈታታቸውና «ይቅርታው» በቀጣዩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሂደት ምን ዓይነት አንድምታ ይኖረው ይሆን? ምንስ ዓይነት አቀባበልና ትርጓሜ ተሰጠው? በሚሉ ጥያቄዎች ዙሪያ የተካሄደ ውይይት ነው።

የውይይቱ ተሳታፊዎች፥ በCalifornia State University የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የህግ ባለ ሞያው ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረ ማርያም፥ አቶ እስክንድር ነጋ፥ የቀድሞ ና እንዲሁም «ወ/ሪት ብርቱካን ነፃ ይለቀቁ፤» ወይም በእንሊዝኛው “Free Birtukan” በሚል መጠሪያ በተለያዩ አገሮችና ልዩ-ልዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ወ/ሪት ብርቱካን እንዲለቀቁ ሲያደርግ በቆየው እንቅስቃሴ የሚታወቀው ቡድን አባል ወጣት ስሂን ኃይሌ ናቸው።

የቀደሙት ሁለት ተወያዮች የወ/ሪት ብርቱካንን መፈታትን ተከትሎ የፃፏቸውን ጨምሮ፤ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በሥፋት ፅፈዋል።