እንግሊዝ ለኢትዮጵያ 219 ሚሊዮን ፓውንድ ልትለግስ ነው

የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት 219 ሚሊዮን ፓውንድ ለመርዳት ዕቅድ እንዳለው አስታወቀ፡፡ ባለፈው ዓርብ ምሽት በእንግሊዝ ኤምባሲ በኢንተርናሽናል ኢንስፓይሬሽን ፕሮጀክት የመግባቢያ ሰነድ ላይ ሲፈረም፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ ምክትል ኃላፊ ሚስተር ክረስ አለን ዕርዳታው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፡፡