አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥርዓተ ፆታ ዲፓርትመንት ተቃውሞ ተነሳበት

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥሩ የሚገኘውንና ብቸኛ የሆነውን የሥነ ፆታ (Gender) የትምህርት ክፍል ሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለስድስተኛ ጊዜ ዋናውን ግቢ ለቅቆ እንዲወጣ በማድረጉ በትምህርት ክፍሉ፣ በሠራተኞችና በተማሪዎች ዘንድ ተቃውሞ ገጠመው፡፡