ናይል ኢንሹራንስ የዓረቦን ገቢው 39 በመቶ ሲያድግ የትርፍ መጠኑ በ2.5 ሚሊዮን ብር ቀንሷል

– ለካሣ ክፍያ 97 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጓል

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ በ2003 የበጀት ዓመት የሰበሰበው ዓረቦን መጠን በ39 በመቶ ሲያድግ፣ ያገኘው የትርፍ መጠን ግን በ2.5 ሚሊዮን ብር መቀነሱ ተመለከተ፡፡