በድህረ ምርጫ 97 ህዳር በወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ ለተጨፈጨፋ ኢትዮጵያውያን ሰማዓታትን ለማስታወስ ዓለም አቀፋዊ ዝግጅት
1. በወርሃ ህዳር በድህረ ምርጫ 1997 የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ድምጻችን ይከበር ብለውና የምርጫውን መጭበርበር ተቃውመው በተስለፉ ንጹሃን ዜጎች ላይ ያካሄደውን ፋሽስታዊ ጭፍጭፋ ምክነያት በማድረግ በግፍ የተሰዉትን የኢትዮጵያ ልጆች ለማስታወስ። በልዩ ልዩ ጊዜያት የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ እምቃ፡ አፈና ፡ግድያ ሰለባ የሆኑ ዜጎችና የፖለቲካ እስረኞች የሚታሰቡበትም ወቅት እንዲሆን፤
2. በዚሁ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ ነጻነት፡ ለፍትህ፡ለህግ የበላይነት፡ ለዴሞክራሲያዊ ሥረዓት በጋራ ለመታገል በዓለም አቀፍ ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያ ከዳር እስከ ዳር ቃል ደግመን የምንገባበት ወቅት እንዲሆን። የእርስ በእርስ ጠለፋዎችና ቅራኔዎች ወደ ጎን ተትተው በመቻቻል ፣ በመደጋገፍና በተሻለ ሁኔታ ትግላችንን በማቀነባበር ትግሉን የምናጠናከርበትም አዲስ ምእራፍና ጅማሮ እንዲሆን፤
3. በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን፡ ታጋይ ድርጅቶች፡ የመገናኛ አውታሮች ሁሉ የትግል የጥቃት ትኩረቶቻቸውን ወደዚህ ወደ ዘረኛ አምባገነናዊ ሥርዓት ብቻ ላይ ያነጣጠረ እንዲሆን፡ ይህም በዓለም አቀፍ ደርጃ የተቀነባበረ የታቀደ እንዲሆን።
4. የኢትዮጵያዊነት፡ የነጻነትና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ጸር ሆኖ ህዝባችንን በአስከፊ ሁኔታ እያፈነ፤እየረገጠና፤እያዋረደ የሚገኘውን ዘረኛና አምባገነናዊ ስርዓትን ለማስወገድ ልዩ ልዩ ተጨማሪ የትግል ስልቶችን በጥናትና በእቅድ ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ለመወጠንና ተግባራዊ ለማድረግ፡፤
5. በወያኔው ዘረኛ አምባገነናዊ አገዛዝ ላይ ጫና የሚያሳድሩ፡ የስነ ልቦና አለመረጋጋት የሚፈጥሩ፡ ልዩ ልዩ የእምቢተኝነትና የአመጽ የትግል ስልቶችን ተግባሪዊ ማድረግ።
6. ሁሉም ዲሞክራሲያዊ ሃይሎችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በጋራ በሚስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ የዓላማና የተግባር አንድነት በመፍጠር በውጭው ዓለም የሚገኘውን መፋዘዝ ፤ለመስበር ተከታታይ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ፡ ትግሉን ለማቀጣጠልና ወደ ሀገር ቤት የሚተላለፉ የመገናኛ ብዙሃን በመጠቀም የኢትዮጵያ ህዝብ የእምቢተኛነት ትግል የሚያካሄድበትን የስነ ልቦና ሁኔታ መፍጠር ፡ የህዝብን ሞራል የሚያነሳሱ ቅስቀሳዎችና እንቅስቅሴዎችን በማድረግ ህዝቡ እንዲነሳሳ ፡ለትግል እንዲነቃቃ ለማድረግ በወያኔው ዘረኛ አምባገነናዊ አገዝዝ ላይ ክፍተኛ ጫና መናጋት የሚፈጥሩ ልዩ ልዩ እርምጃዎችን መውሰድ።
7. በወርሃ ህዳር ውስጥ በየአካባቢው መደርግ የሚገባቸው ተግባራት እንደየህገሩና አካባቢው ሁኔታ በግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረጉ ሊሆኑ ይችላሉ።
ህ) ህዝባዊ ስብስባዎች
ለ) የሻማ ማብራት (ቪጅል)
ሐ) ህዝባዊ ሰልፎች
መ) በቤተ አምልኮዎች ጸሎትና ምህላ
ሠ) አትዮጵያውያን በብዛት በሚያዘወትሩባቸው አካባቢዎች በራሪ ወረቀቶች ማሰራጨት
8. በዓለም አቀፍ ግብረሃሉና በየሀገሩና በአካባቢው የሚገኙ ኮሚቴዎች የሚከተሉትን ተግባራዊ ያደርጋል፦
ሀ. የህዝቡን ትኩረት ወደዚህ ዝግጅት ለማድረግ ሁሉም ደህረ-ገጾች ስለሰማዓታቱና ስለ ወያኔ አጠቃላይ ወንጀሎች ተከታታይ ልዩ ልዩ ቪድዮች እንዲያወጡ ፤ ልዩ ልዩ ድርጅቶች መግለጫዎች እንዲያወጡ፤
ለ. በሬድዮኖች በወርሃ ህዳር የወያኔ ጭፍጨፋና የተሰውት ሰማዓታት አስመልክቶ እንዲሁም በተያያዘ የትግል ጉዳዮች ዙሪያ ግማሽ ፕሮጋራማቸውን እንዲያውሉ።
– ርአሰ አንቅጾች
– ሀተታዎች
– ቃለ-ምልልስ
– ከልዩ ልዩ ታጋዮች የዓይን እማኞችና የፖለቲካ ሰዎች ጋርሐ. በፓል -ቶኮችም ተመሳሳይና ተከታታይ ፕሮግራሞች ማድረግ
መ. ምሁራኖችና ታዋቂ ጸሃፊዎች በዚሁ ዙሪያ ልዩ ልዩ ጽሁፎች እንዲጽፉ
ሠ. የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ቅስቀሳ ቃለ ምልልስ እንዲያደርጉ
ረ. ኢትዮጵያውያን ዜጎች በየቦታው፡ ቤተ ክርስትያን ፡መስጊድ በሌሎች ቦታዎች ሁሉ ሰማዓታት የሚታስቡበት ሁኔታ መፍጠር ፡ ቅስቅሳ ማድረግ