ከሁዋላ የበቀለ ቀንድ ጆሮን ይቀድማል (መንግስቴ ደፋር)
ከአቶ/ሮ አዜብ ጌታቸው በጋ . . . “ኢሕአፓዎች ዛፍ ያጣ ጉሬዛ አትሁኑ” በሚል ርዕስ የተፃፈውን ጽሁፍ ተመለከትኩት። ከጽሁፍ የተረዳሁት ነገር ቢኖር፣ ወደ ደጀሰላም ዝክር በአክብሮት የተጠራ ሰው፣ የሚገባውን ያህል ከተቋደሰ በሁዋላ፣ ሂሳብ ለማወራረድ እንደሚታገል ጀብራሬ የተወላገደ የነጠላ ዜማ ቅኝት መሆኑን ብቻ ነው። ብዕርዎ የገዛ ምስልዎን የሚቀርጹበት መሮ መሆኑን ደግሞ አይዘንጉት። “ አንድ አለብህ ይላል ያገር ቤት ዘፋኝ”