የቀድሞ የሜጋ ኪነ ጥበባት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

– ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ተፈቀደለት

(በታምሩ ጽጌ)

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስና የገቢ ግብር ባለመክፈል ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው፣ የቀድሞ የሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል ሥራ አስኪያጅና የኢትዮጵያ ኦዲዮ ቪዥዋል አሳታሚዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዕቁባይ በርኸ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡