የኃየሎም አርአያ አሟሟት እውነተኛ ታሪክ እና የጀሚል ያሲን መጨረሻ
(ዳዊት ከበደ ወየሳ – ከአትላንታ)
አንዳንድ ጊዜ የኃየሎም አርአያ ጉዳይ ሲነሳ እንባ የሚተናነቃቸው ሰዎች አጋጥሞኛል። እንባ እየተናነቃቸው ሻዕቢያ ያስገደለው መሆኑን ይናገራሉ። “የለም ኃየሎምን ጀሚል እንጂ ሻዕቢያ አለረገደለውም።” በሚል ንዴት ሊያፈጡባችሁ የሚችሉ ሰዎች አሉ። እኔ ብዙ ጊዜ አጋጥሞኛል። እውነተኛውን ታሪክ ስነግራቸው ግን እሳት የሚተፉ አይኖቻቸው እንባ ያዝላሉ።አሁንም ይህንኑ ቃል ብደግመው የሚናደዱ ሰዎች ይኖራሉ። የማውቀውን እውነት እንድናገር ግን ፍቀዱልኝ… ከዚያ የራሳችሁን ፍርድ ስጡ።