ፓትርያርክ መርቆሬዎስ የት ነሁ? ብጹእ መልከ-ጼዴቅስ?
ካምፓላም ታመመ፡ ታመሰ እኮ !!
ተክለሚካኤል፡ አበበ (ቶሮንቶ)
የዛሬ አስር ወር አካባቢ ለግል ጉዳይ ወደ ዩጋንዳ ተጉዤ ነበር። አንድ የፌብሩዋሪ 2011 የመጀመሪያ ሰንበት ጠዋት ወካምፓላ መካነሰላም መድሀኔዓለም ቤተክርስቲያን አመራሁ። ባጋጣሚ ከአገልግሎት በኋላ ምርጫ ነበርና አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ ሲያደርግ፡ ሪፖርት ሲቀርብና የሰዎች ስም ዝርዝር ቀርቦ፡ ሰዎቹ በቤቱ ሲጸድቁ ታዝቤያለሁ። በሰዓቱ፡ በገንዘብ ሪፖረት እንዲሁም በቀጣይ አመት በጀት ላይ ከተነሱ አንዳንድ ጥያቄዎች በስተቀር፡ ምርጫውን ተቃውሞ ምንም አይነት የሚያነታርክ ነገር ተነስቶ ሀሳብ ሲሰጥ ወይንም ሲከራከሩ አልተመለከትኩም። እነሆ ጉዳዬን ጨርሼ ወደሰሜን አሜሪካ ከተመለስኩ በኋላ ግን፡ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ብጥብጥ እንደተጀመረና፡ ሰዉ በሁለት ተቧድኖ እየተነታረከ እንደሆነ ሰማሁ።