ካየሁት ከማስታውሰው – ልዑል ራስ እምሩ ሃይለ ሥላሴ (ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ)
የልዑል ራስ እምሩ ሃይለ ሥላሴን “ካየሁት ከማስታውሰው” እያነበብኩ አስቀድሞ በተመሳሳይ ዘመን ታሪክ ዙሪያ ባጠነጠኑ ኦቶባዮግራፊዎች ላይ ያነበብኳቸውና አልፎ አልፎ ያልተብራሩልኝ አልያም የደበዘዙብኝ ግዙፍ የታሪክ ሁነቶችንና ደግሞም እማላውቃቸውን ክስተቶችን ራስ እምሩ እያፍታቱ፤ እያበራዩ፤ እየገላለጡ … ሲያወጉ ባገኛቸው ጊዜ፤ ነፍስያዬ ተመስጣ ጣቶቼም ገፅን በገፅ እያጣፉ ስፈተለክ፤ ስሜቴ ደግሞ አንዴም በአግራሞት፤ አንዴም በመቆዘም…ይናወጥብኝ ነበር። እንዴትና ለምን? ብሎ መጠየቅ መቼም አግባብ ነው። መልሱንም በሁለት ቃላት መቋጨት አይከብድም – መጥ ፉን ማንበብ – በሚል። ካየሁት ከማስታውሰው – (ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ)