ጓሳ – ያልተዘመረለት ተፈጥሮ
…አቶ መለስ “መሀል ሜዳ” የመጡ ጊዜ ታድያ ሰውየው ያረፉበት ስፍራ “ሕይወት ሆቴል” በሚባል አነስተኛ የገጠር መዝናኛ መሆኑ ተነግሮኝ ይህንኑ ለማረጋገጥ ሄድኩኝ፡፡ ሆቴሏ በከተማዋ መሀል ትገኛለች፡፡ ሙሉ በሙሉ የጭቃ ቤት ስትሆን ጥግ ጥጉን የተሰሩ ወደ ጎን ያዘመሙ መኝታ ክፍሎችና አንድ ምግብ ቤት በውስጧ ይዛለች፡፡ የሆቴሉ እመቤት የሀበሻ ቀሚስ አድርገው፣ ግዙፍ መነፅራቸውን ደቅነው ለምሳ ቤታቸው የተገኘውን ሰው ለማብላት ተፍ ተፍ ሲሉ አገኘኋቸው፡፡…
ደብረብርሃን፣ ባኬሎ፣ ጣርማ በር፣ መዘዞ፣ ማዞርያ፣ ጓሳ፣ መሀል ሜዳ፡፡ እነዚህ ወዳልተዘመረለት የጓሳ ምድር የሚያደርሱ የኢትዮጵያ ትንንሽ ከተሞች ናቸው፡፡ አዲስ አበባን መነሻ ካደረግን 260 ኪሎ ሜትር መራቅ ይኖርብናል፡፡ ይህ ድንቅ ስፍራ እንደ አክሱም ሽቅብ የተቀሰረ ሀውልት የለውም፤ እንደ ላሊበላ በፍልፍል ድንጋይ አልታነፀም፤ እንደ ኤርታሌ የሚንተከተክ ላቫ አልፈጠረበትም፡፡ እንዲያው ዝም ብሎ የተዘረጋ የፕላቶ ሸንተረር ነው፡፡ ግን ልብን ወከክ የሚያደርግ፣ ቢያዩት ቢያዩት የማይጠገብ እንዲሁም የማያልቅ፣ እንዲሁም የማይደክም ግን ደግሞ ሩቅና ሰ…ፊ!
ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ወይም ወደ የአማርኛውን ክፍል ይጎብኙ።