የወ/ት ብርቱካን ዳግም ይቅርታና ፋይዳው – አስቴር ተሾመ

የአንዴነት ፓርቲ ፕሬዚዯንት ወይዘሪት ብርቱካን ሜዯቅሳ ከሃያ አንዴ ወራት የግፍና ህገወጥ እስራት በኋሊ ሰሞኑን ተፈትተዋሌ። በዚህም ኢትዮጵያዊ ወገናቸው፣ ቤተሰባቸውና ፕሬዚዲንቷ የፖሇቲካ ሰሇባ መሆናቸውን ተረዴተው እንዱፈቱ ሲታገለሊቸው የነበሩ ዓሇም አቀፍ ዴርጅቶች፣ መንግሥታትና በመሊው ዓሇም የሚኖሩ የውጭ አገር ሰዎች ተዯስተዋሌ፤ የዯስታ መግሇጫም አውጥተዋሌ። ዯስታው ግን ቁጭት የተዯባሇቀበት በመሆኑ የዯበዘዘ ነበር። ሇዚህም ምክንያት አሇው። ብርቱካን ከመጀመሪያውም ቢሆን ሉታሰሩ የማይገባቸው ንጹህ ሰው መሆናቸውን ሁለም ስሇሚያውቅ በውስጡ የታመቀው ቁጣና ንዳት አሁንም እንዲሇ ነው። ከህግ ውጭ መታሰራቸው አሌበቃ ብል፣ የእስረኛ መብታቸውን ተገፈው በጨሇማ ክፍሌ ውስጥ ከሀያ አንዴ ወሮች በሊይ ያሳሇፉትን የሰቆቃና የስቃይ ጊዜ በቀሊለ መርሳት የሚቻሌ አሌሆነም። እንዯአሳሪዎቻቸው ቂመኛነትና ኢሰብዓዊነት፣ ጭቦኛነትና ጥሊቻ ያሌተጠናወታቸው፣ ሀቅንና ንጹህ ህሉናን የተሊበሱ ወጣትና የመጀመሪያዋ እንስት መሪ መሆናቸውን ህዝቡ አውቆ ተስፋ ጥልባቸው ስሇነበር በተፈጸመው ግፍ የዯማው ሌቡ ገና አሌጠገነም። በትምህርትና በሌምዴ ያዲበሩት የህግ ሙያቸው ሇህጋዊነት የቆሙ የህግና የፍትህ ጠበቃ፣ ፍጹም ሰሊማዊ ሰው ሆነው ሳሇ፣ በሀሰት መንግሥት የሇጠፈባቸውን የወንጀሇኛነት ስም ከጥቂት ካዴሬዎቹ በቀር ማንም ሉቀበሌሇት አሌቻሇም። ይግረማችሁ ብል፣ ከእግር ጣት እስከአናቱ ዴረስ በዓይነትና ብዛት ወዯር በላሇው ወንጀሌ የተዘፈቀው ይህ መንግሥት፣ እኒህን ወጣት የህግ ባሇሙያና የሰሊም አርበኛ ወንጀሇኛ ብል ፈርጇሌ። በዚህም የቆሰሇው የሳቸውና የላልች በሚሉዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የፍትህ ስሜት እንዲይሽር፣ አሁንም በመሰሪ ፕሮፓጋንዲው እየጓጏጠ እንዱያመረቅዝ ማዴረግ መቀጠለን ማንም አሌወዯዯሇትም። ይባስ ብል ይቅርታ ተብየው ይዞት የወጣው መግሇጫ መንግሥት የታወቀበትን መሰሪነትና ወንጀሇኛነት እንዯገና ይፋ ከማዴረጉ በቀር አዴማጭ ጆሮ ሉያስገኝሇት አሌቻሇም። ብርቱካን የቂም፣ የጭካኔና የማንአሇብኝነት ስሜት ማብረጃ ሆነው የወረዯባቸው የአካሌና/ ወይም የኅሉና ሰቆቃ (torture) ድፍ ያሊስቆጨውና ያሊስቆጣው የሇም። የነዚህ ሁኔታዎች ዴምር ውጤት ነው ከእስር በመፈታታቸው ሰፍኖ የነበረውን ዯስታ እንዱዯበዝዝ ያዯረገው።

አብዮታዊ ዱሞክራቱ መሇስ የብርቱካን ችግር የጤንነት አሇመሟሊት ሳይሆን የክብዯት መጨመር ነው እያለ ሲያፌዙ ተሰምተዋሌ። ወ/ት ብርቱካንን ከወህኒ የሇቀቋቸው ግን ክብዯት ጨምረው ሳይሆን ጠውሌገው፣ ክብዯት ቀንሰውና ዯክመው ነው። ጠ/ሚኒስትሩ በሚያጠራቀሙት የውሸት ክምር ሊይ በተጨማሪ የመቆሇሊቸው ምስጢር የማይገባ ቢሆንም፣ በየጊዜው በሚናገሩት ውሸት ህዝባቸው እንዲሌተመቸውና የሀፍረት ስቃይ እንዯገጠመው ዯፍሮ የሚመክር ባሇሟሌ በመጥፋቱ እሳቸው በዋሹ ቁጥር ከመበሳጨትና ከማፈር መሊቀቅ አሌቻሌንም።

በ1997 ዓ. ምቱ. ምርጫ ቅንጅት ማሸነፉን፣ ወ/ት ብርቱካን ከህጋዊና ሰሊማዊ የትግሌ አጋሮቻቸው ጋር ታስረው እንዱማቅቁ መዯረጉና በመጨረሻውም ‚በካንጋሮ ፍ/ቤት‛ የተወሰነባቸው ያሊግባብ መሆኑን ብዙ ህዝብ ያምናሌ። መንግሥት በሽምግሌና ተይዞ ያሇቀሇትን ጉዲይ ሆን ብል በመጎተት ጥፋተኛ አሰኝቶ በዕዴሜ ሌክ ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ካስዯረገ በኋሊ በገዯብ በሚሰጥ ይቅርታ የጠንካራ ተቀዋሚ መሪዎችን እንቅስቃሴ መግታት ወይም ማስቆም የሚችሌበትን ሰይጣናዊ ስሌት ነዴፎ አስቀምጧሌ። ይህም በቀጣይነት በይቅርታ የወጡ ተቀዋሚ መሪዎችን በዕዴሜ ሌክ ጽኑ እስራት ግርሻ እያስፈራራ ሇማዲከም ወይም ሇማስወገዴ የሚያስችሌ ወጥመዴ አጥምድ ‚ጠሊቱ‛ የመሰሇውን ጠንካራ ተቀዋሚ ሇማነቅ አቆብቁቦ እንዱጠብቅ የሚያስችሇው ነው። የዚህ ተንኮሌና ሴራ የመጀመሪያ ሰሇባ የሆኑት በጠንካራ ተፎካካሪነት በመውጣት ሊይ የነበሩት ወ/ት ብርቱካን ናቸው። ‚አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብሊኝ‛ እንዲሇችው እንስሳ ሰበብ ፈሌጎ ባዘጋጀው ወጥመዴ ባይገቡም ገብተዋሌ ብል በግፍና ከህግ ወጭ አሰራቸው። ወዯሁሇት ዓመት ሇሚጠጋ ጊዜም አሰቃይቶና የሚፈሌገውን ሁለ ፈጽሞ ሇቀቃቸው።

ወ/ት ብርቱካን ከተፈቱበት ዕሇት ጀምሮ የተፈቱበት ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኗሌ። ከ‚ፍትህ ሚኒስቴር‛ የወጣ ነው ተብል በመንግሥት መገናኛ አውታሮች የተሰራጨው መግሇጫ በርካታ ጥያቄዎችን አስነስቷሌ። መግሇጫው እንዯተሇመዯው የመንግሥትን አቋም የሚዯግፍና ወይዘሪቱ ጥፋታቸውን አምነው ዲግም ይቅርታ ሰሇጠየቁ እንዯተፈቀዯሊቸው የሚግሌጽ ነው። መንግሥት ይህን ከመግሇጽም አሌፎ፣ በእስርና በኅሉና ስቆቃ ያጎሳቆሊቸውን ሴት ስብዕና እና ዯጋፊዎቻቸውን ሉያሳዝን፣ ምናሌባትም ሉከፋፍሌ ይችሊሌ በሚሌ እሳቤ፣ በተጽዕኖ ተፈርሞ የቀረበሇትን የይቅርታ ማመሌከቻ ሇፕሮፓጋንዲ ጠቀሜታው እንዱውሌ አዴርጓሌ። አንዲንዴ ሰዎች አይበገሪዋ ወ/ሪት ብርቱካን እንዳት ይህን የመሰሇ ይዘት ያሇው ማመሌከቻ ሉጽፉ ቻለ? ማሇታቸው አይቀርም። ጥያቄው መነሳቱ ተገቢነት አሇው። ሇጥያቄው የሚሰጠው ምሊሽ ግን ሁኔታውን ከስሜታዊነትና ችኩሌነት ነፃ በሆነ መንፈስ በጥንቃቄና በርጋታ መርምሮና መዝኖ ትክክሇኛ መዯምዯሚያ ሊይ የሚያዯርስ መሆን አሇበት። በመሰረቱ ወ/ት ብርቱካንን የገጠማቸው ሀይሌ (ጠሊት) በአምባገነንነት የታወቀ፣ የማሰቃየትና የመግዯሌ ታሪክ ያሇው፣ በትእቢትና በማንአሇብኝነት የፈሇገውን ሲያዯርግ ጠያቂ የላሇበት፣ ሇህግም ሆነ ሇፍትህ ቁብ የላሇው፣ በሥሌጣኔ አትምጡብኝ ብል የመከሩትን ወዲጅ መንግሥታት ሳይቀር የጠሊ መንግሥት እንዯመሆኑ፣ እውነትን በመያዝ ህግና የፍትህ ተቋማት ይጠብቁኛሌ በሚባሌበት ሁኔታ ሊይ አሌነበሩም። የመከራ ገፈቱን ከቀመሱት ከባሇቤቷ የበሇጠ የተሰቃየና የሚያውቅ የሇም። በተሇይ እሳቸው የነበሩበትን የተራዘመ የሰቆቃ፣ የእንግሌትና የጨሇማ ህይወት ሳንቀምስና ሳናይ በተመቸና ነፃ አካባቢ በመኖር ምን ማዴረግ ይገባቸው እንዯነበር ሇመምከርም ሆነ አስተያየት ሇመስጠት መዴፈር ራሱ አሳፋሪ ነው። ብቃቱም የሇንም። ከዴርሻቸው በሊይ ሇህዝባቸውና ሇሀገራቸው መስዋእትነት ከፍሇዋሌ። ላሊውን ከመተቸታችን በፊት እኔስ ምን አዯረግሁ? ሇሚሇው ጥያቄ ትክክሇኛ መሌስ እንፈሌግ። በኔ እምነት የፖሇቲካ ህይወታቸውን በማይገዴብና በማይጎዲ ሁኔታ፣ አሳሪያቸው እንዲዯረገው የፈሇገውን ፈጽመው መሊቀቅና እጅግ ወዯሚፈሌጋቸው የትግሌ መስክ መቀሊቀሊቸው ብሌህነትና ተገቢ ነው፡፡ አሳሪያቸው በፈሇገው ዓይነት እንዱፈርሙ ማስገዯደ የሚያጋሌጠው አሳሪውን ራሱን እንጂ፣ የሳቸው ፊርማም ሆነ በነፃ ያሌተገኜ ቃሌ ሀቁን እንዯማይሇውጠው ወዯፊት እናያሇን። በእሌህ ሇሀቅ ስሌ ታስሬ እኖራሇሁ ቢለ የሚጎደት ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን የሚመሩትንም ዴርጅትና ህዝባቸውን ጭምር ነው። በሳሌ አመራራቸውን በመስጠት ዴርጅታቸውን እንዱያጠናክሩና ሇዴሌ እንዱያበቁ ዴርጅታቸውና የኢትዮጵያ ህዝብ አጥብቀው ይፈሌጓቸዋሌ። በእስራት ምክንያት ከአመራር ውጭ መሆናቸው የጠቀመውና የሚጠቅመው ገዥውን ፓርቲ ብቻ ታስረው መቆየታቸው በፍጹም ጎጅ ነው።

በፈረጠመ የመንግሥት ጡንቻና አፈሙዝ ሰር የወዯቁት ብርቱካን የፈረሙትን ፈርመው መውጣታቸው ሇትግለ አጋዥነት ያሇውን ትክክሇኛ እርምጃ በመውሰዲቸው ወዯአሸናፊነት ሉያያንዯረዴራቸው የሚችሇውን የመጀመሪያና ትክክሇኛ ውሳኔ ነው ያዯረጉት። መውዯቅና መነሳት፣ መሸነፍና ማሸነፍ ያሇ ነው። አሳፋሪ ነገር ሰርቶ የተሸነፈ ነው ማንሰራራት የማይችሇው። የአኩሪና አንጸባራቂ ታሪክ ባሇቤት ሆኖ በግፈኞች መታሰርና መሰቃየት ግን ሇትግለ አጋዥና ዴሌንም የሚያቃርብ መሆኑ በታሪክ የተረጋገጠ ነው። እሳቸው በከፈለት መስዋዕትነት በዓሇም አቀፍ ዯረጃ ሳይቀር ይበሌጥ ተዋቂነትን አተረፉበት እንጅ፣ አሳሪዎቻቸው እንዲሰቡት ዝናቸውንና መሌካም ስማቸውንም በአንዴ ጠባብ ክፍሌ አስሮ ማስቀረት አሌቻለም፤ እንዱያውም በዓሇም እንዱናኝ ሆኗሌ።

ከሊይ እንዯተጠቆመው፣ ወ/ት ብርቱካን ይህን ማዴረግ ነበረባቸው፣ የሇም አሌነበረባቸውም ብሇን የምንከራከርበት ጊዜ ሊይ አይዯሇንም። በማይጠቅመን ጭፍጫፊ ጉዲይ እንዴንወዛገብና እንዴንከፋፈሌ ነው ገዥው ፓርቲ ሆን ብል ይህን መሰሌ የመወዛገቢያ የቤት ሥራ የሚሰጠን። ወጥመደ ውስጥ ሌንገባሇት አይገባም። ተቻኩሇን የየራሳችንን ፍርዴ ከመስጠት መጠንቀቅ ይኖርብናሌ። ግራና ቀኙን መመርመር፣ ጥቅምና ጉዲትን ማየት፣ በሚገባ ሳይጤን ተቻኩሇን የምንወስዯው አቋም ሉያስከትሌ የሚችሇውንም ውጤት ማሰብ ያስፈሌጋሌ። ሁሌጊዜም ሇምንሇው መሇኪያ አዴርገን መውሰዴ ያሇብን እኛኑ ራሳችንን ሉሆን ይገባሌ። በአጭሩ ራሳችንን በብርቱካን ቦታ በማሰቀመጥ እንዯብርቱካን ታስሬ እየተሰቃየሁ ያሇሁ ሰው ብሆን ኖሮ እሳቸው ካዯረጉት ውጭ ምን ማዴረግ እችሌ ነበር? ብሇን ራሳችንን መጠየቅ ይገባሌ። ርግጥ ነው ይህ ምናባዊ በመሆኑ የሳቸውን ስቃይ እስካሌቀመስን ዴረስ ትክክሇኛው መሌስ ሊይ መዴረስ ያዲግተን ይሆናሌ። እስካሌታሰርንም ዴረስ እንዯታሰረው ሰው የነፃነት ትርጉምና ዋጋም በውሌ ሉገባን አይችሌም ይሆናሌ። ግን ሁሊችንም የምንስማማበት በኢትዮጵያ በተሇይ የፖሇቲካ እስረኛ ነፃነት፣ የዯህንነትና የህይወት ዋስትና በላለበት ሁኔታ የሚኖር መሆኑ ነው።

ወ/ት ብርቱካን ነፃነት፣ የዯህንነትና የህይወት ዋስትና በላሇበት ሁኔታና ቦታ ሊይ የነበሩ። በመሆናቸውም ከሳቸው ዴርጊት፣ ባህርይና ተፈጥሮ ጋር በማይጣጣም አገሊሇጽ ራሳቸውን ‚ህዝብንና መንግሥትን አታሌያሇሁ‛ ብሇው እንዱዘሌፉ ተገዯዋሌ። የአሳሪዎቻቸው ዯስታና ፍሊጎት ‚ጠሊት‛ በሚሎቸው ሰዎች ስቃይ መዯሰትና የፖሇቲካ ትርፍ ሇማግኘት መቆመር ነው። ይህ ጊዚያዊ ርካታን ቢያስገኝሊቸውም ታሪክ ጊዜውን ጠብቆ ሀቁን ያወጣሌ። ቆይቶ መሊቀቅ የማይችለት አሸማቃቂ ነውርና እንከን ይሆናሌ።

እንዯወ/ት ብርቱካን ሇመሰሇን ሀቀኛ ሰው ያሌሆነውን ሆኛሇሁ፣ ያሊዯረገውን አዴርጊያሇሁ ብል እንዱፈርም የማስገዯዴ ዓሊማና ግብ ግሌጽ ነው። የወ/ት ብርቱካንን አይበገሬነትና ጥንካሬ ያሊሊሌ፣ ሞራሊቸውን ይነካሌ፣ ዯጋፊዎቻቸውን ይከፋፍሊሌ፣ ቅስማቸውንም ይሰብራሌ ከሚሌ እሳቤ እና ብርቱካን የታሰሩት ያሊግባብ ነው የምትለ ሁለ ባሇቤቷ ያመኑትን እናንተ ሌትክደት አትችለም ብል የተሇመዯ የጭቦ ከበሮ ሇመዯሇቅ ነው።

የመንግሥቱ መግሇጫ ወ/ት ብርቱካን ‚ወዯዚህ ስህተት ሉገቡ የቻለት ‘መንግሥት የውጭ ኃይልችን ተፅዕኖ በመፍራት ሉያስረኝ አይችሌም፤ ካሰረኝም ተገድ በአጭር ጊዜ ይፈታኛሌ’ በሚሌ የተሳሳተ ግንዛቤ መሆኑን የገሇፁ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን የተሰጣቸውን ይቅርታ በመካዴ የኢትዮጵያን ሕዝብና መንግሥት በማታሇላ ከፍተኛ ፀፀት ተሰምቶኛሌ…‛ ብሇው ይቅርታ እንዱዯረግሊቸው ጠይቀዋሌ ይሊሌ። እዚህ ሊይ የሚነሱ ነጥቦች አለ። በጥቅሱ የተገሇጸውን ወ/ት ብርቱካን ብሇው ሉሆን ይችሊሌ። ከእስር ሇመፈታትና ከስቃይ ሇመገሊገሌ የቀረበሊቸው ብቸኛ አማራጭ የተጠቀሰውን እንዱለ የሚያስገዴዴ ከሆነ ማሇታቸውን እስማማበታሇሁ። ግን ግሌጽ መሆን ያሇበት አንዴ ነገር አሇ። ወይዘሪይቱ የተጠቀሰውን በማሇታቸው እውነቱን ተናግረዋሌ ማሇት አይዯሇም። አውቀው ዋሽተዋሌም ማሇት አይዯሇም። አሳሪዎቻቸው የፈሇጉትና ከእስር መሇቀቅ የሚያስችሊቸው እውነቱን መናገር ሳይሆን እነሱ የሇመደትን ውሸት እንዱቀበለ ማስገዯዴ በመሆኑ በእውነቱ ቦታ ውሸት እንዱተካ ተዯርጓሌ የሚሌ ጽኑ እምነት አሇኝ። ይህ የብርቱካንን ባህርይና ሀቀኝነት ጥያቄ ሊይ የሚጥሌ አይዯሇም – በትክክሌ ከሳቸው ነፃ ኅሉና በፍሊጎታቸው የመነጨ ትክክሇኛ ቃሊቸው አይዯሇምና። ዝቅ ብየ እመሇስበታሇሁ።

በተሇይ ብርቱካን ‚መንግሥት የውጭ ኃይልችን ተፅዕኖ በመፍራት ሉያስረኝ አይችሌም፡፡ ካሰረኝም ተገድ በአጭር ጊዜ ይፈታኛሌ’’ ብሊ ነው የተዲፈረችው የሚሇው አገሊሇጽ አቶ መሇስ በተዯጋጋሚ የገሇጹትን እንዱያረጋግጥ ሆን ተብል የገባ ይመስሊሌ። እንዱያውም ማመሌከቻው በሳቸው ተረቆ በዚህ ሊይ ካሌፈረመች እዚያው በስብሳ ትቀራሇች፣ ማንም ሉያስፈታት አይችሌም ተብል የተሊከ ያስመስሇዋሌ። በተጨማሪም ይህም አብዮታዊ ዱሞክራቱ መሪያችን ይለ የነበረው ትክክሌ መሆኑን ከራሷ ከብርቱካን ስሙት የሚሌ መሌዕክት ሇማስተሊሇፍና የመሪውን ተክሇ-ስብዕና personality cult ሇመገንባት የተጀመረው እንቅስቃሴ አካሌ ይመስሊሌ።

በመሰረቱ ወ/ሪት ብርቱካን ከመታሰራቸው በፊት ነፃ ሆነው ‚ቃላ‛ በተሰኘው ታሪካዊ መግሇጫቸው የተነተኑት በህግ፣ በስነ-አመክዮ (ልጅክ)፣ በማስረጃና ሁለ ሰው በሚያውቀው እውነታ የተዯገፈ እውነተኛ ቃሊቸው መሆኑን የሚጠራጠር አይኖርም። ‚ቃላ‛ ሊይ የሰፈረው ሀሳብ ሇመከሊከሌ ብሇው ያቀረቡት ክርክር አይዯሇም። በሳቸው ባይነሳም ኖሮ እንዯሳቸው ጣዕምና ውበት መስጠት ባይቻሌም ጉዲዩን አጣርቶ መጽፍ የሚሞክር ማንም ሰው ሉያነሳው የሚችሌ ሀቅ ነው። በይቅርታ ማመሌከቻው ሊይ የተገሇጸውና ‚ቃላ‛ ሊይ የሰፈረው ሀሳብ የሚቃረንና የማይገናኝ ነው። የትኛው ነው እውነቱ? ሇሚሇው ጥያቄ መሌሱ ቀሊሌ ነው። ሇኔ ነፃ ሆነው በራሳቸው ፍሊጎት መነሻና መዴረሻውን በመተንተን በሚያሳምን ሁኔታ በ‛ቃላ‛ ሊይ የጻፉት፣ በእስር ሰቆቃና እንግሌት እየተሰቃዩ ማንም ምስክር በላሇበት፣ ቢኖርም እንኳን ነፃ መሆንን በማያሳይበት ሁኔታ ሇይቅርታ ቅዴመ-ሁኔታው ራስሽን መንግሥትንና ህዝብን አታሌያሇሁ ብሇሽ ፈርሚ ተብሇው ከፈረሙት የበሇጠ ሙለ በሙለ ያሳምነኛሌ።

ወ/ት ብርቱካን ይቅርታ መጠየቃቸውን ክዯው አያውቁም። ቃላ በተሰኘው መግሇጫቸውም ሊይ ይቅርታ መጠየቃቸውን አምነዋሌ። በህግ ባሇሙያነታቸው ያነሱትና ላልችም አብረዋቸው ታስረው የነበሩ ሲናገሩ የሚሰማው የይቅርታ አጠያየቅ ስርዓቱ የይቅርታ አዋጅ በሚጠይቀው መንገዴ የተካሄዯ አሌነበረም፣ በሽምግሌና በተዯረገው ዴርዴር መሰረት ማመሌከቻው ከጥፋተኛነት ውሳኔ በፊት ተጽፎ የተፈረመ ነው የሚሌ ነው። ይህም የስነ ስርዓት አሇመጠበቅን ሇመግሇጽ የተሰነዘረ አስተያየት እንጂ ይቅርታ መጠየቃቸውን የካዯ አባባሌ አይዯሇም። ሇታሪክ ጸሀፊዎች የይቅርታ ጠያቂዎቹ ማመሌከቻ፣ የፍትህ ሚኒስቴር ሰነድችና ቃላ ህያው ምስክሮች ናቸው።

ሀቁ ይህ ሆኖ ሳሇ፣ ወ/ት ብርቱካን ‚የተሰጠኝን ይቅርታ በመካዴ የኢትዮጵያን ህዝብና መንግሥት በማታሇላ ከፍተኛ ፀፀት ተሰምቶኛሌ‛ ብሇዋሌ፣ የሚሇው የመንግሥት መግሇጫ ከእውነት ጋር መሄዴ አይችሌም። እንዯእውነቱ ከሆነ በስሌጣን በመባሇግ፣ ሀሰት መሆኑን እያወቀ እውነት ሇማስመሰሌ በተጽዕኖ ሀሰተኛ ቃሌ እንዱሰጠው አስገዴድ በመቀበሌ ይፋ አዴርጎ ህዝብን እያሳሳተ ያሇው መንግሥት በመሆኑ ህዝብን አታሎሌ። ይቅርታ መጠየቅ የሚገባው እሱ ነው።

ከሊይ እንዯተገሇጠው ዲግም ይቅርታ ጠያቂዋ የቀዴሞውን ይቅርታ አሌካደም እንጅ ቢክደ እንኳን ዴርጊታቸው የኢትዮጵያን ህዝብና መንግሥት ማታሇሌ አይሆንም። ዴርጊታቸው የህግንም ሆነ የተሇመዯውን የማታሇሌ ትርጉም የሚያሟሊ አይሆንም። ህዝብንም መንግሥትንም አሊታሇለም። ካሊታሇለ ዯግሞ የሚሰማቸው ‚ከፍተኛ ፀፀት‛ ሉኖር አይችሌምና ዲግም ይቅርታ የሚያስጠይቅ አይዯሇም። በአንዴ ‚ጥፋት‛ ሁሇት ይቅርታ! የመጀመሪያውም ይቅርታ የተሻረበት ስርዓት የይቅርታ አዋጅ ከሚጠይቀው ውጭ መሆኑን ብዙ ባሇሙያተኞች በተሇያየ ጊዜ የተቹበት ነው.።

መንግሥት በተሇያዩ የዓሇም ክፍልችና በሀገር ውስጥ በዯረሰበት ተጽዕኖ፣ እንዱሁም የፖሇቲካ ዓሊማውን በማሳካቱ ምክንያት ወ/ት ብርቱካንን መፍታት ግዴ ይሆንበት ነበር። አቶ መሇስ ከገቡበት አጣብቂኝ መውጣት የሚያስችሊቸው እንዯተሇመዯው የሀገር ሽማግላዎችን መሊክና በስቃይ የተጎሳቆለትን ወ/ት ብርቱካንን በማሳመን ጠ/ሚኒስትሩ በፈሇጉት ሁኔታ እንዱጠናቀቅ ማዴረግ ነበር። የፈሇጉትን አግኝተዋሌ። ውጤት የሚያመጣሊቸው ግን አይሆንም። ወ/ት ብርቱካንን ጥፋተኛ አስመስል ይቅርታ እንዱጠይቁ የተተበተበው ሁለ ከተጨባጭ እውነታው ጋር አይሄዴምና። ይህንና በተሇይ ኢህአዳግ የፈጸመውንና የሚፈጽመውን ዯባ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃሌና። ይህም በመሆኑ በወ/ት ብርቱካን ሊይ የተተበተበው ርካሽ የውሸት ዴሪቶ ወንዝ አያሻግርም፣ ምክንያቶቹም ውሀ ሉቋጥሩ አይችለም።

በወቅቱ የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ እውነተኛ ፍርዴ የሚሰጥ ነፃ ፍርዴ ቤት ስሇላሇ ፍርዴ ሰጭም ሆነ ነፃ አውጭ ህዝብ ነው። ያሊግባብ እንዯታሰሩ የሚያውቀው ህዝብ ዲግም ይቅርታ የሚያስጠይቅ ጥፋት እንዲሌፈጸሙ ስሇሚያውቅ ወ/ት ብርቱካን ይቅርታ እንዱጠይቁት አይጠብቅም። ይሌቁንስ በተንኮሌና በግፍ አስሮ ያሰቃያቸው መንግሥት ወ/ት ብርቱካንን ይቅርታ ሉጠይቅ በተገባው ነበር።

የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያነሳኋቸውን ነጥቦች ራሳቸው ወ/ት ብርቱካን አሁን ባለበት ሁኔታ ሉያነሷቸው አይችለም። ምናሌባት ሀቁን የሚናገሩበት ጊዜ አሁን ሊይሆን ይችሊሌ፣ ግን ሩቅ አይሆንም። የተፈቱበት የይቅርታ ቅዴመ ሁኔታ እውነት ሇመናገር ሊይፈቅዴሊቸው ይችሊሌ። እውነቱን ቢናገሩ የፈጸምኩት ጥፋት የሇም በማሇት ‚ቃላ‛ ሊይ የገሇጹትን አቋም እንዯገና መግሇጽ ነው የሚሆነው። ይህ ዯግሞ ጥፋትሽን አምነሽ ይቅርታ አሌጠየቅሽም ነበር ማሇት ነው ተብሇው ሇሶስተኛ ጊዜ ወዯወህኔ ቤት እንዱሊኩ ያስዯርጋቸዋሌ። ስሇዚህ በዚህ ነጥብ ሊይ ሇጊዜው ከሳቸው ብዙም መጠበቅ የሚቻሌ አይመስሌምና እሳቸውንም እንዱያወጡ መወትወት አይገባም።

ብርቱካን በኢትዮጵያ ህዝብና በታሪክ ነፃ ሆነው ይኖራለ።

[email protected]