ጋዳፊ በምስጢር በተያዘ ቦታ ሊቢያ ውስጥ ተቀበሩ
የሙአመር ኧል ጋዳፊ ቀብር እና የደጋፊዎቻቸው አስተያየት
የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ኧል ጋዳፊ በሊቢያ በአንድ በምሥጢር በተያዘ ቦታ መቀበራቸው ተገለጸ። ጋዳፊ፣ ልጃቸው ሙዋታሲም እና የመከላከያ ሚንስትራቸው አቡ በከር ዩኒስ ጃበር ጥቂት ቤተዘመድ እና የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ንጋት ላይ በእሥላማዊው ኃይማኖት ደንብ መሠረት ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙን የሽግግሩ ብሔራዊ ምክር ቤት አስታውቋል።