በካምፓላ መድኀኒያለም ቤ/ክርስቲያን ውዝግብ ቀጥሏል

አቡነ ኤልያስ ጉዳዩን በቅጡ ሳያጠኑ አንዱን ወገን ደግፈዋል!

ሰባት ምእመናን ታስረው ተፈቱ!

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 19 ቀን 2004 ዓ.ም. October 30፣ 2011)፦ በአፍሪካ ካሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አቢያተ ክርስቲያናት በምእመናን ብዛትና ጥንካሬ አንዱ በሆነው ዩጋንዳ – ካምፓላ በሚገኘው የመካነ ሰላም መድኀንያለም ቤተክርስቲያን በምእመናንና በጥቂት የቀድሞ የሰበካ ጉባኤ አባላት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ቀጥሏል።