ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተከሰሰ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ያለምክንያት ምዝገባ ከልክሎኛል” በሚል ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ለኢትዮጵያዊነት ፓርቲ (ሕዝባዊ) የተባለ አዲስ የተቋቋመ የፖለቲካ ፓርቲ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰባተኛ ፍትሐ ብሔር ልደታ ምድብ ችሎት ክስ ቀረበበት፡፡