የአስካሉካን ባለቤት የዋስትናና መረጃ ማሰባሰብ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ
ለመጀመርያ ጊዜ በአፍሪካ አኅጉር በተዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ውድድር በርካታ ሰዎችን ደቡብ አፍሪካ ለመላክ የገባውን ቃል ባለመፈጸም በወንጀል የተከሰሰው፣ የአስካሉካን ትሬዲንግ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ግርማይ ገብረ ሚካኤል፣ ባለፈው ረቡዕ በተከሰሰበት የከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ልደታ ምድብ ችሎት በመቅረብ፣ በዋስትና ወይም በአጃቢ ፖሊስ ወጥቶ መረጃ ለማሰባሰብ ቢያመለክትም በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ፡፡