ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ‹‹የእስር ጊዜዬ አስጨናቂና ከባድ ነበር›› አሉ
– ስለ ቀጣይ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው ጊዜ ወስደው እንደሚወስኑ አስታወቁ
(በታምሩ ጽጌ)
ከድጋሚ የዕድሜ ልክ እስራት መንግሥትን ይቅርታ በመጠየቅ ከ19 ወራት የማረሚያ ቤት ቆይታ በኋላ መስከረም 26 ቀን 2003 ዓ.ም. የተፈቱት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ የነበሩበት የእስር ሁኔታ በጣም አስጨናቂና ከባድ እንደነበር ገለጹ፡፡