የጭለማ ቤት ጓደኞቼ
ሲሳይ አጌና
ልክ የዛሬ አምስት ዓመት በጥቅምት 1999 ዓ.ም. ዓለም በቃኝ ጭለማ ቤት የነበሩት የጭለማ ቤት ጓደኞቼ ዛሬ ተመልሰው ጨለማ ቤት ከወደቁ አንድ ወር አስቆጠሩ፤ ለመብት እና ለነጻነት መቆም፣ ለእውነት እና ለፍትህ መሰለፍ፣ እኩልነት እና ዲሞክራሲ መጠየቅ በወንጀል ተመንዝሮ፣ በአሸባሪነት ተፈርጆ ወህኒ ወርደዋል። ክሱ የፈጠራ፣ ሁሉ ነገር የጨበጣ እንደሆነ ከመነሻው ግልጽ የሆነው የህወሓት መሪዎች ውሸታሞች መሆናቸው ስለሚታወቅ ብቻ አልነበረም፤ …