ሞገደኛው መለስና፤ የሰላማዊ ትግል ተስፋና እውነታ (ክፍል – 2 የመጨረሻ)

ሉሉ ከበደ

የግንቦት 2007 ምርጫ ወያኔ በከፍተኛ አደጋ ላይ ያለ መሆኑን አመልክቷል። የኢትዮጵያን ህዝብ ለውጥ ፈላጊነት በከፍተኛ ደረጃ ያመለከት፤ ህዝቡ ለወያኔ ገዢ ቡድን ለጠባብ ዘረኝነት ርዕዮት ዓለም የጠለቀ ጥላቻ እንዳለው የገለጸ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መለስ ዜናዊ እንደገመተው ያልተከፋፈለ መሆኑን ያረጋገጠ፤ ከጦርነት ይልቅ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ዘመኑ የሚፈቅደው የፖለቲካ አካሄድ መሆኑን ህዝቡ ጠንቅቆ የተረዳ መሆኑን ወያኔ ራሱ የተረዳበት፤ የወያኔ ባዶነት የተገለጸበትና ሞራሉ እስከመጨረሻው የወደቀበት የታሪክ ምእራፍ ነበር።