በኢትዮጵያ ስለሀገር መፀለይም ያስወነጅላል
ይሄይስ አዕምሮ
በቅድሚያ ውድ ልጃችንና እህታችን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከጠባቡ እስር ቤት ወጥታ ወደ ሰፊው እስር ቤት እኛው ዘንድ በመቀላቀልዋ የተሰማኝን ደስት በዚች አጋጣሚ እንድገልጽ ይፈቀድልኝ። እንኳን ደስ ያለን! … መፈታትዋ ትልቅ ነገር መሆኑ እንዳለ ሆኖ ትግሉ ተጀመረ እንጂ ገና እልባት ስላላገኘ በመለስተኛ ደስታ ዋንውን ድል እንደማንዘነጋ ሁሉአችን ይንጋራው እምነት መሆኑን እረዳለሁ።