አንድነት ፓርቲ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አቤት አለ

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የታሰሩት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አመራር አባላት በቅርብ ዘመዶቻቸው፣ በጓደኞቻቸውና በሐኪሞቻቸው የሚጐበኙበትን ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተከታትሎ እንዲያስፈጽም አንድነት ፓርቲ ጠየቀ፡፡