በፑንትላንድ ሞት የተፈረደበት ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች መንግሥትን እየተማፀኑ ነው

•    ከሞት ለመትረፍ እስከ ዓርብ 700 ሺሕ ብር መክፈል አለበት

ከሶማሊያ ተገንጥላ ራሷን በምታስተዳድረው ፑንትላንድ ውስጥ በምትገኘው ቦሳሶ ከተማ የሞት ፍርድ የተፈረደበትን ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች፣ መንግሥት እንዲያተርፍላቸው እየተማፀኑ ነው፡፡