ጊብሰን ትምህርት ቤት ወደቀድሞው የማስተማር ሥርዓት እንዲመለስ ተወሰነበት

ጊብሰን ዩዝ አካዳሚ ትምህርት ቤት ከወላጆች ጋር ሳይመካከር ከመስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከአምስተኛ ክፍል በላይ ባሉ ተማሪዎች ላይ ፆታን መሠረት ያደረገ ክፍፍል ማድረጉን ተከትሎ፣ ከወላጆች በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከቦሌ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር፣ ትምህርት ቤቱ ቀድሞ ወደነበረበት የማስተማር ሥርዓቱ እንዲመለስ ወስነውበታል፡፡