የሃላባ ብሔረሰብ የ13 ዓመት የማንነት ጥያቄ ወደ ግጭት እያመራ ነው
“ግጭቱ የሃላባና የሃዲያ የሚባል ሳይሆን የግለሰብ ነው” የሃዲያ ዞን ምሥራቅ ባዳዋቾ አስተዳዳሪ
ላለፉት 13 ዓመታት “እኛ ሃላባዎች እንጂ ሃድያዎች አይደለንም፤” በሚል የማንነት ጥያቄ ሲያነሱ የቆዩት በሃዲያ ዞን ውስጥ የሚገኙ ሦስት ወረዳዎች፣ ጥያቄያቸው ምላሽ በማጣቱ ወደ ግጭት በማምራት ላይ መሆናቸውን ገለጹ፡፡