የሙአመር አል ጋዳፊ መጨረሻና አዲሲቱ ሊቢያ

ላለፉት 42 ዓመታት በጭካኔያቸው፣ ወጣ ባለው ባህርያቸውና በአወዛጋቢነታቸው የሚታወቁት የቀድሞው የሊቢያ መሪ ኮሎኔል ሙአመር ሙሐመድ አቡ ሚኒያር አል ጋዳፊ፣ ባለፈው ሐሙስ በትውልድ ከተማቸው ሲርት አቅራቢያ ከተማረኩ በኋላ እስካሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡