ህልም ሆኖም አይቀርም። አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ
እየሮጠ ጊዜው ለእኛም ሊነጋጋ፤
ታየኝ ከጋዳፊ ነፃነት ተጠጋ።
ሞት ይመርጣል እንጂ ሕዝቡማ አይምርም??
የራበው ነፃነት፦
ህልም ሆኖም አይቀርም።
ቃዠን ሃያ ዓመታት፦ራዕይ ጥበቃ፤
መለስ ነው ተረኛ ጋዳፊም አበቃ::
እኛም አልን በቃ፤
ብርጥቆ ከነቃ፡
አይሆንም ለዕቃ::
እናም ገዬ በቃ!!!!
እንነሳ በቃ!!!
ሕዝብ አይታለልም ባመፁ አይምርም፤
እንንቃ ከቅዠት ህልም ሆኖ አይቀርም።
በሰበብ እንውጣ ይህ አጋጣሚ ነው ፤
መጥቷል አዲሱ ለውጥ:-
በደም የታገልነው።
አትነሳም ወይ “አትነሺም ወይ”፤
በግፍ መገዛት አይበቃንም ወይ???
ሞት ቆሞ የሚጠራው፤
የመለስ ነው ተራው።
ቆራጡ ኢትዮጵያዊ፤
ከጀመረ አይምርም፤
ያለመው ነፃነት፦
ቅዠት ሆኖ አይቀርም;
የራበው ነፃነት፦
ህልም ሆኖም አይቀርም።