የሸበሌ ትራንስፖርት ሠራተኞችና ኃላፊዎች በሙስና እየተወዛገቡ ነው
– ጉዳዩን ፀረ ሙስና ኮሚሽን እየመረመረው ነው
(በብርቱካን ፈንታ)
ከፕራይቬታይዜሽንና ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ አንዱ ከሆነው ሸበሌ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር፣ አምስት ተሽከርካሪዎችን ከሕግና ከደንብ ውጭ ያለጨረታ በመሸጣቸው ሙስና ተፈጽሟል በሚል ኃላፊዎችና ሠራተኞቹ እየተወዛገቡ ነው፡፡