የአዲሱ ካቢኔ አባላት ሹመት ፀደቀ

* አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆኑ

(በጋዜጣው ሪፖርተር)

በዛሬው ዕለት መስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም. በዋለው የተወካዮች ምክር ቤት ሁለተኛ ስብሰባ የካቢኔ ዕጩዎች ሹመት የፀደቀ ሲሆን፣ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡