የአርኪዮሎጂ ተመራቂዎች ትምህርት ሚኒስቴር ሊቀበለን ፈቃደኛ አይደለም አሉ
‹‹የዩኒቨርሲቲዎች ፍላጐት እስከሌለ ድረስ ልንመድባቸው አንችልም›› ትምህርት ሚኒስቴር
ለመጀመርያ ጊዜ በአርኪዮሎጂ የትምህርት ክፍል በ2003 ዓ.ም. ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ 32 ተመራቂዎች መካከል ለአስተማሪነት አልፋችኋል የተባሉ 14 ምሩቃን፣ ትምህርት ሚኒስቴር ሊቀበላቸው አለመቻሉን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡