አቶ ያረጋል አይሸሹም ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ

የቀድሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ያረጋል አይሸሹም፣ ያለመከሰስ መብታቸው በትናንትናው ዕለት ተነሳ፡፡