የትራንስፎርሜሽኑ መዘዝ

ይሄይስ አዕምሮ ([email protected])

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለዘመናት ጨንፍሮ ከያዛት ድህነት ለማላቀቅ የኢህአዴግ መንግሥት የትራንስፎርሜሽን ዐዋጅ በቅርቡ ማወጁ የሚታወቅ ነው። ጥሩ መመኘት ጥሩ ነው። ዐዋጁ እንደስካሁኖቹ የግብር ይውጣና የማሞኛ ዐዋጆች ሆኖ የማይቀር ከሆነ ሀገርና ህዝብ ለሽዎች ዓመታት ተዘፍቀውበት ከነበሩበት የድህነት አዘቅትና የችግር አዙሪት መውጣታቸው ከሰይጣን በስተቀር የማያስደስተው ስለሌለ ሁላችንንም እሰየው የሚያሰኝ ዕፁብ ድንቅ ነገር ነው።