አቶ አባዱላ ገመዳ የፓርላማው አፈጉባዔ ሆኑ

መሰከረም 24 ቀን 2003 ዓ.ም. በተካሄደው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዙር ጉባዔ፣ አቶ አባዱላ ገመዳ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ሆነው ተመረጡ፡፡
አቶ አባዱላ ገመዳ ከ541 ተመራጮች የ540 መራጮችን ድምፅ አግኝተዋል፡፡
በምክትል አፈ ጉባዔነት ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ በድጋሚ ተመርጠዋል፡፡