መንግሥት ዘንድሮ ከብሔራዊ ባንክ እንደማይበደር አስታወቀ

መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረው ገንዘብ የዋጋ ግሽበትን እንደሚያስከትል በመገንዘቡ፣ በያዝነው ዓመት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብድር ላለመውሰድ የወሰነ መሆኑን ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ አስታወቁ፡፡