ኢህአዴግ በሶማሌ ላንድ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ስደተኞች እንዲታፈሱለት ጠየቀ
300 የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስደተኞች በሀርጌሳ ታስረዋል
Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 27 ቀን 2004 ዓ.ም. October 8, 2011)፦ የኢህአዴግ መንግስት በሱማሌ ላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ስደተኞች ታፍነው እንዲመለሱለት ትእዛዝ አስተላልፏል። በዚህም መሰረት እስካሁን 300 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአሰሳ ተይዘው በሀርጌሳ እስር ቤቶች ውስጥ የታጎሩ ሲሆን በቅርቡም ወደ አዲስ አበባ ይላካሉ ተብሏል።