ለሚሊኒየም ፓርክ እንዲሆን የተከለለው ቦታ ለካድሬዎችና ለግለሰቦች መሰጠቱ በጥናት ተረጋገጠ

በደቡብ ክልል ጋሞጎፋ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ የሚገኙ 548 የላንቴ ቀበሌ አባወራዎች በተወካዮቻቸው አማካይነት ከሁለት ሳምንት በፊት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት አቤቱታ፣ በ2000 ዓ.ም. ለሚሊኒየም ፓርክ እንዲሆን የተከለለው ቦታና ለዘመናት ሲጠበቅ የቆየው ጥብቅ ደን እየተመነጠረ ለካድሬዎችና ለግለሰቦች አየተሰጠ ነው አሉ፡፡