የኦሮሚያ ሰሌዳ ያላቸው ሦስት ሺሕ ሚኒባሶች ከአዲስ አበባ እንዲወጡ ታዘዘ

–  ‹እናንተ ተቸግራችሁ ለእኛ ብቻ ስጡን ማለት አይቻልም›› የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ባለሥልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ ተከስቶ የነበረውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩት የኦሮሚያ ሰሌዳ ያላቸው ሦስት ሺሕ ሚኒባሶች፣ ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲመለሱ መታዘዙን የኦሮሚያ ትራንስፖርት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡