ድርጅታዊ መበስበስ፣ ጥገኝነት እና አድርባይነትን መዋጋት ያቃተው የኢህአዴግ የ”መተካካት” ድራማ
በአህመድ አባጊሣ
ልባቸውን የናጠ ግን እንደ እባብ ያስቀጠቀጣቸው ግጥም
በውቧ የባህር ዳር ከተማ ቀደም ባለው እና አስከፊውን የደርግ ሥርዓት መንግሎ ለመጣል በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ግንባር ቀደም ሚና ስለተጫወቱ እንደ ሙሉዓለም እጅጉ ያሉ ታጋዮች በአንድ አለብላቢ ምላስ ባለው ካድሬ አማካይነት የሰሙት ግጥም ደስ ብሏቸዋል – ወደ 1200 የሚጠጉ በከተማዋ በሚገኘው የተንጣለለው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የታደሙ የንቅናቄው አባላት።