በማዕከላዊ 78 የሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ታስረዋል
– ደበበ እሸቱ ቤተሰቦቹን በበቂ ሁኔታ ማግኘት አልቻለም
የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አባል የሆኑት አቶ ኦልባና ሌሊሳና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ፣ በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ 78 ግለሰቦች በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) መታሰራቸውን ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብዓዊነት መብት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡