‹‹ልዩ ድጐማ የሚያገኙ የመንግሥት ተቋማት እውነተኛና ጠንካራ ተወዳዳሪ አይሆኑም›› አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ፣ የኅብረት ኢንሹራንስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር
አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ የኅብረት ኢንሹራንስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናቸው፡፡ በዚህ የኃላፊነት ቦታ ላይ 17 ዓመታትን አስቆጥረዋል፡፡ የዚህ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና አደራጅና በግለሰብ ደረጃ በኩባንያው ውስጥ ትልቅ ነው የሚባለውን አክሲዮን ከያዙት ግለሰቦች መካከል አንዱ ናቸው፡፡