አዘራፊና ዘራፊ ሲበላ ባለ አገር ይቀላውጣል (አስራደው – ከፈረንሳይ)

ወያኔ በጎሣ በረት ያጎራቸው የአስተሳሰብ ዴንክዬዎች፤ በታጎሩበት የጎሣ በረት ውስጥ ሆነው ሲያጓሩ ስንሰማ፤ እኛ እንደነሱ በዘረኝነት ታጥረን ሳይሆን፤ በኢትዮጵያዊነት ማማችን ላይ ሆነን ቁልቁል ስንመለከታቸው፤ እያንጋጠጡ የሚተፉት ሁሉ ተመልሶ ባፋቸው እየገባ፣ አረፋ ሲደፍቁ ስናይ፤ አዘንላቸው እንጂ አልጨከንባቸውም። ታዘብናቸው እንጂ አልከፋንም። ይበልጥ አበረቱን እንጂ ክንዳችን አልዛለም። ብዕራችን አንደበቱ ሳለ እንጂ አልተዘጋም።