“ልጄ እንደ አባቱ የነፃነት ታጋይ እንደሚሆን አምናለሁ” ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል
ማስታወሻ፦ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል የታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ነች። በምርጫ 97 ወደ ወህኒ ቤት ከተላኩት ጋዜጠኞች ውስጥም አንዷ ነበረች። ወደ 18 ወራት በእስር ቤት ቆይታለች። የወለደችውም በወህኒ ቤት በታሰረችበት ወቅት ሲሆን፣ ሕፃኑ ሲወለድ ከክብደት በታች በመሆኑ ማሞቂያ ወይንም ኢንኩቤተር ውስጥ እንዲገባ በፖሊስ ሆስፒታል ሐኪሞች ተወሰነ። የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ግን ሥልጣናቸውን በመጠቀም ሕፃን ናፍቆት እስክንድር ማሞቂያ ውስጥ እንዳይገባ ፈረዱበት።