በዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ኢትዮጵያ አዳዲስ የቡና ገበያዎችን እየፈለገች ነው

የአሜሪካና የአውሮፓ ኢኮኖሚ ለሁለተኛ ጊዜ አዘቅት ውስጥ እየገባ መሆኑን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሆነው ቡና ገበያ እንዳያጣ መንግሥትና የቡና ነጋዴዎች አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን በመፈለግ ሥራ ላይ ተጠምደው ሰንብተዋል፡፡