28 ቢሊዮን 469 ዶላሩ የት ገባ? 384 ቢሊዮን ብሩ ማለቴ ነው!

ሲሳይ አጌና – ከአዲስ አበባ

ቀጣዩ ቀልድ ከዚህ ጽሁፍ ይልቅ “በውሸት ደዌ ለምትሰቃዩ – እነሆ ዕውነቱ!..” በሚል ርእስ ቀደም ሲል ነሀሴ ላይ ለለቀቅኩት ፅሁፍ ይበልጥ የሚስማማ ይመስለኛል፤ ሆኖም ቀልዱን አንድም በወቅቱ ላስታውሰው ባለመቻሌ፤ በሌላ በኩል ይህ ጽሁፍ ምንም እንኳን በዋናነትበአለም አቀፍ እርዳታዎች ላይ ቢያተኩርም እንደ ቀጣይ ክፍል ሊወስድ የሚገባው በመሆኑ፤ በሶስተኛ ደረጃ ግንኙነት ባይኖረው እንኳን ቀልዱን ያልሰማችሁ ብትሰሙት ማለትም ብታነቡት ምን ጉዳት አለው? በሚል ከሱ ልጀምር።