“የፖለቲካ አስረኞቹ በአስቸኳይ ይፈቱ!” በሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ሰጭ ማኅበር
Ethiopia Zare (ዓርብ መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ.ም. September 23, 2011)፦ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ “ከሽብርተኞች ጋር ንክኪ አላቸው” የሚል መሰረተ ቢስ ክስ እየመሰረተ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራር አባላትን፣ የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞችንና አርቲስቶችን ወደ እስር ማጎሩን አስመልክቶ በሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ሰጪ ማኅበር ትናንት ባወጣው መግለጫ እስረኞቹ ባስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።