ይድረስ ለጂጂ – “የጎበዝ ወዳጅ”
ደጉ ታዬ ([email protected])
ለጂጂ
እጅጋየሁ (ጂጂ) … አንቺ አሁን መብራት ሆንሽ። በወታደሮቹ ቋንቋ አብሪ የሚባል ነገር አለ። ቀዳሚ እንደማለት ነው። ድሮ በነበላይ ዘለቀ፣ በነአብዲሳ አጋ፣ በነኡመር ሰመተር እና በነኃይለማሪያም ማሞ አገር ደግሞ ዘፈኑም የሚለው ይሄንኑ ነው። የጎበዝ ወዳጅ ታስታውቃለች ይባላል። ”በቃ!” በማለትሽ “የጎበዝ ወዳጅ” ሆንሽ ማለት ነው።