”የታሰሩት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች አባላቶቼ አይሉም” ግንቦት 7

Ethiopia Zare (ረቡዕ መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም. September 14, 2011)፦ ባለፈው መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም. የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አንዷለም አራጌንና ሌሎች ሦስት የፓርቲውን የምክር ቤት አባላትና እውቁን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላቸው በማለት ኢህአዴግ ያሠራቸው ግለሰቦች ”ከእኔ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም” በማለት ግንቦት ሰባት መግለጫ አወጣ።