በመስከረም ወር አዲስ አበባ ውስጥ የደረሰውን ፍንዳታ ያቀነባበረውና የፈጸመው ሽብርተኛው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ እንደነበር ዊኪሊክስ አጋለጠ

መስከረም ወር ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ለሶስት ሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነውንና በርካታ ንብረት ያወደመውን የቦምብ ፍንዳታ ያቀነባበረውና ሴራውንም የሸረበው ዘረኛውና አጥፊው የወያኔ አገዛዝ ቁንጮ መለስ ዜናዊ እንደነበር በዊኪ ሊክስ ላይ አፈትልኮ የወጣው የአሜሪካ መንግሥት መረጃ አጋለጠ።

በወቅቱ በአዲስ አበባ ፍንዳታ በደረሰበት ወቅት ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በቁጥጥሩ ስር በሚገኙት የቴሌቪዥንና ራዲዮ ጣቢያዎች ፍንዳታውን የፈጸሙት የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ሽብርተኞች ናቸው በማለት በርካታ ኢትዮጵያዊያንን ወደ እስር ቤት ማስገባቱና ማሰቃየቱንም ዊኪሊክስ አክሎ ገልጹአል።ይሁን እንጂ ከአሜሪካን ኤምባሲ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ፍንዳታውን ያቀነባበረውና ቦምቡንም እንዲፈነዳ ያደረገው ራሱ የወያኔ አገዛዝ ሳይሆን እንደማይቀር መግለጹ ታውቁአል።

በአዲስ አበባ ከተማ በካራቆሬ ክፍለ ከተማ የደረሱትን ሶስት ተከታታይ ፍንዳታዎች በሚመለከት ቦምቡን ያጠመዱትም ሆነ ያፈነዱት የኢትዮጵያ በዲሞክራሲያዊ ጎዳና መገስገስና በልማት መበልጸግ የሚያንገበግባቸው ሽብርተኞች ናቸው በማለት የዘረኛው አገዛዝ ባለስልጣናት ሪፖርት አድርገው እንደነበር ዊኪሊክስ አጋልጦአል።

ዊክሊክስ ይፋ ባደረገው በዚህ ሪፖርት የተቀነባበረው ፍንዳታ ባዲስ አበባ ከተማ በደረሰበት ወቅት ዶ|ር መራራ ጉዲና ፍንዳታውን ያቀነባበረውም ሆነ ያፈነዳው ራሱ የወያኔ አገዛዝ ነው በማለት ቃለ ምልልስ ማድረጋቸውን ጨምሮ ገልጾአል።

ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳው የወያኔ አገዛዝ በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች ከተሞች የተለያዩ ፍንዳታዊኦች እንዲደርሱ ያደረገና በፍንዳታዎችም ሰበብ በርካታ ንጹሃን ዜጎችን እስር ቤት በማጎሩ የሚታወቅ ሲሆን፣ ኢትዮጵያዊያን የወያኔን ደባና ተንኮል አበጥረው እንደሚያውቁና ሽብርተኛውም ማን እንደሆነ በግልጽ ሲናገሩ እንደእነበር መዘገባችን ይታወሳል።