ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የዩሪያና ዳፕ ማዳበሪያ ፋብሪካዎችን ሊገነባ ነው

–  በዋጋ መናር ምክንያት የማዳበሪያ ጨረታ ተሰረዘ

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በአገሪቱ የመጀመሪያ የሚሆኑትን ሁለት የማዳበርያ ፋብሪካዎችን ለመገንባት የሚያስችለውን ስምምነት፣ ከፕራይቬታይዜሽንና ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ጋር ሊፈራረም መሆኑን ምንጮች አመለከቱ፡፡