ሙገር አዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካ እንዲገነባ ታዘዘ

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት መጀመርያ ሲያካሂድ የቆየውን የሲሚንቶ ፋብሪካ ማስፋፊያ ግንባታ ያጠናቀቀው ሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝ፣ እያመረተ ከሚገኘው የሲሚንቶ መጠን በእጥፍ የሚያመርት አዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካ እንዲገነባ ትዕዛዝ ተሰጠው፡፡