የክራር ንግስቷ አስናቀች ወርቁ በ76 ዓመቷ አረፈች

የቀብር ስነ ስርዓቷ ነገ በስላሴ ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል

Ethiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 4 ቀን 2004 ዓ.ም. September 15, 2011)የክራሯ ንግስት በመባል የምትታወቀው አንጋፋዋ የመድረክ ባለሙያ አስናቀች ወርቁ 76 ዓመቷ ለረዥም ጊዜ በህክምና ስትረዳ ከቆየች በኋላ ህይወቷ ማለፉ ተገለጸ።